Indiana 988

የመርጃ መሳሪያ

ስለ 988 ግንዛቤ ለሌሎች በማስጨበጥ Hoosiersን ያግዙ

በኢንዲያና በሚገኙት በሁሉም 92 ካውንቲዎች ውስጥ የ 988 ን የራስን ማጥፋትና ቀውሶች የሕይወት አድን ድጋፍ መልዕክት ለሌሎች ማጋራት ለኛ አስፈላጊ ነው። ለጓደኞችዎ፣ ለቤተሰቦችዎ፣ ለአባላቶችዎ እና ለእርስዎ ባለድርሻ አካላት የ988 መልእክትን ለማስተዋወቅ የሚጠቀሙበትን የሚከተሉትን የመርጃ መሳሪያዎች አዘጋጅተናል። ከዚህ በታች ያለውን ይዘትና መልእክት የያዙት የመርጃ መሳሪያዎች ሊያወርዷቸውና ይህን አስፈላጊ መልእክት ለማሰራጨት ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ። በመላው ግዛት ግንዛቤ ለማስጨበጥ እንዲቻል የበኩልዎን እገዛ ለማድረግ በቀላሉ የኢሜይል ናሙናዎችን፣ የጽሑፍ መልእክቱን ቅጂ እና ግራፊክሱን በቀላሉ ይቅዱና ይለጥፉ። ተጨማሪ የመርጃ መሳሪያዎች ስለሚዘጋጁ ብዙ ጊዜ ምን አዲስ ነገር እንዳለ ያረጋግጡ።

በአገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጁ መርጃዎችን ለማግኘት እባክዎ SAMHSA toolkitን ይጎብኙ።

የኢሜይል ቅጂ

የሚከተለው ቅጂ Hoosiersን ስለ 988 የህይወት አድን ድጋፍ (Lifeline) ለማሳወቅ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።

ጉዳዩ፦ ስለ የ 988 ራስን ማጥፋትና ቀውስ የሕይወት አድን ድጋፍ ግንዛቤ ለማስጨበጥ እገዛ ስለማድረግ

ዉድ [name]፣

988 ወደስኬት የሚመራ ነው። ለእርስዎ የሚደርስልዎትና ያለምንም ትችትና ነቀፌታ የሚያስፈልግዎትን እገዛ የሚሰጥዎት የሆነ ሰው አለ። ባስፈለግዎት ጊዜ የሚፈልጉት፣ ማንኛውም አይነት እርዳታ ነው።

988 ከራስን ማጥፋት፣ ከአእምሮ ጤና ወይም ከአደገኛ ዕፅና መድኃኒት አጠቃቀም ቀውስ ወይም ሌላ ማናቸውም አይነት የስሜት ጉዳት ጋር የተገናኘ የአእምሮ ጤና ጉዳት ላጋጠመው ሰው ርህራሄን የተሞላ፣ በቀላሉ ተደራሽ የሆነ እንክብካቤና የድጋፍ ቀጥተኛ ግንኙነትን ያቀርባል።

ስለ 988 ራስን ማጥፋትና ቀውስ የሕይወት አድን ድጋፍ ግንዛቤን ለማስጨበጥ እንዲረዳ የኢንዲያና የቤተሰብ እና የማኅበራዊ አገልግሎቶች አስተዳደር የአስረጃ ስብስቦችን አዘጋጅቷል። ጠቃሚ ማስረጃዎችን እዚህ ላይ ይገኛሉ።

እርስዎ ራስዎ ወይም ሌላ የሚያውቁት ሰው ከአእምሮ ጤና ጋር የተገናኘ ችግር ወይም በአደገኛ ዕፅ ወይም መድኃኒት የተነሣ ችግር ካጋጠማቹነ ተስፋ እንዲሁም እገዛ ማግኘት ይችላሉ። ራስን ማጥፋትና ቀውስ የሕይወት አድን ድጋፍ ለማግኘት በሙያው ከሠለጠነ የቀውስ ልዩ ባለሙያ ጋር በቀን 24 ሰዓት በሳምንት 7 ቀን ለመነጋገር ወደ 988 ይደውሉ ወይም የጽሑፍ መልእክት ይላኩ።

አመሰግናለሁ!

የጽሑፍ መልእክት ቅጂ

የሚከተለው ቅጂ Hoosiersን ስለ 988 ራስን ማጥፋትና ቀውስ የሕይወት አድን ድጋፍ ለማሳወቅ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።

በአሁኑ ጊዜ እርስዎ ራስዎ ወይም ሌላ የሚያውቁት ሰው ራስን የማጥፋት ሃሳቦች ወይም የአእምሮ ጤና ወይም በአደገኛ ዕፅ ወይም መድኃኒት አጠቃቀም ችግር እያጋጠማቹ ከሆነ ራስን ማጥፋትና ቀውስ የሕይወት አድን ድጋፍ ለማግኘት ለማግኘትና በሙያው የሰለጠነ የቀውስ ልዩ ባለሙያ ጋር ለመነጋገር እባክዎ ወደ 988 ይደውሉ ወይም የጽሑፍ መልእክት ይላኩ። 988 ወደ ስኬት የሚመራ ሲሆን በሚፈልጉበት ጊዜ ያለምንም ትችትና ነቀፌታ የሚያስፈልግዎትን ድጋፍ የሚሰጥ ነው።

ማሕበራዊ ሚድያ ቅጂ

በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ግራፊክስን አጅቦ ለማቅረብ ከዚህ በታች ያለውን ቅጂ ይጠቀሙ።

አማራጭ 1

988 ምንድን ነው?

988 ወደ ስኬት የሚመራ ነው። ለመረዳት የሚያዳምጥ ነው። እገዛ ለማግኘት የመጀመሪያው ምዕራፍ ነው። የሚረዳዎት የሆነ ሰው ነው። ምን እንደሚያስፈልግዎት በማያውቁበት ጊዜ የሚያስፈልግዎ ማንኛውም ነገር ነው። እርስዎ ወይም የሚያውቁት ሰው ከአእምሮ ጤና ጋር በተገናኘ ችግር ውስጥ እያለፋችሁ ከሆነወደ 988 ራስን ማጥፋትና ቀውስ የሕይወት አድን ድጋፍ ይደውሉ ወይም የጽሑፍ መልእክት ይላኩ።

አማራጭ 2

988 ምንድን ነው?

988 ለማስታወስ ቀላል የሆነ ቁጥር ከመሆኑበላይ ብዙ ቁምነገር አለው። ራስን ማጥፋት ሃሳቦች፣ ጭንቀት፣ ድባቴ፣ከአደገኛ ዕፅና መድኃኒት አጠቃቀም ወይም ሌላ ማናቸውም የስሜት ጉዳት ጋር የተገናኘ ማናቸውም የአእምሮ ጤና ጋር የተገናኘ ቀውስ ላጋጠመው ሰው ርህራሄን የተሞላ፣ በቀላሉ ተደራሽ የሆነ እንክብካቤና የድጋፍ ቀጥተኛ ግ ንኙነትን ያቀርባል።

ግራፊክስ፦ 1080 x 1920

የሚከተሉት የማኅበራዊ ሚዲያ ግራፊክሶች ይበልጥ በ ኢንስታግራም እና በፌስቡክ ጥቅም ላይ ይውላሉ። ኮምፒውተርዎ ላይ አንድን ምስል ለማስቀመጥ ከምስሉ በታች በቀኝ በኩል ጠቅ ያድርጉ (በ Mac ኮምፒውተር ላይ Control+Click ይጠቀሙ)።

ግራፊክስ፦ 1080 x 1080

የሚከተሉት የማኅበራዊ ሚዲያ ግራፊክሶች ይበልጥ በ ኢንስታግራም እና በፌስቡክ ላይ ጥቅም ላይ ይውላሉ። ኮምፒውተርዎ ላይ አንድን ምስል ለማስቀመጥ ከምስሉ በታች በቀኝ በኩል ጠቅ ያድርጉ (በ Mac ኮምፒውተር ላይ Control+Click ይጠቀሙ)።

ግራፊክስ፦ 1200 x 675

የሚከተለው የማኅበራዊ ሚዲያ ግራፊክሶች ይበልጥ በ ትዊተር ላይ ጥቅም ላይ ይውላሉ። ኮምፒውተርዎ ላይ አንድን ምስል ለማስቀመጥ ከምስሉ በታች በቀኝ በኩል ጠቅ ያድርጉ (በ Mac ኮምፒውተር ላይ Control+Click ይጠቀሙ)።

መታተም የሚችሉ ፖስተሮች

ለማተም እና ለማጋራት የሚከተለው ፖስተር እና በራሪ ወረቀት አማራጮች ተፈጥረዋል። ገጾቹን በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማውረድ ከታች ያለውን ምስል ጠቅ ያድርጉ።

እገዛ አሁኑኑ ያግኙ።

በአሁኑ ጊዜ እርስዎ ራስዎ ወይም ሌላ የሚያውቁት ሰው ራስን የማጥፋት ሃሳቦች ወይም፣ የአእምሮ ጤና ወይም በአደገኛ ዕፅ ወይም መድኃኒት አጠቃቀም ችግር እያጋጠማችሁ ከሆነ ራስን ማጥፋትና ቀውስ የሕይወት አድን ድጋፍ ለማግኘትና በሙያው የሰለጠነ የቀውስ ልዩ ባለሙያ ጋር በቀን 24 ሰዓት በሳምንት 7 ቀን ለመነጋገር እባክዎ ወደ 988 ይደውሉ ወይም የጽሑፍ መልእክት ይላኩ።